Calais Migrant Solidarity
Anti-Raids
Barnardo's
Stop G4S
Stop Deportations
Press Action
Past campaigns
በዩናይትድ ኪንግደም (እንግሊዝ) ውስጥ እገዛ ለማግኘት የሚያስፈልጉ የስልክ ቁጥሮች
በዩናይትድ ኪንግደም (እንግሊዝ) ውስጥ እገዛ ለማግኘት የሚያስፈልጉ የስልክ ቁጥሮች
1. ነጻ የሕግ መረጃ እና የምክር አገልግሎት በራስ ቋንቋ ለማግኘት
የስደተኛ ኮሚቴ ካውንስልን (በጎ አድራጎት ድርጅት)
በስልክ ቁጥር 08088082255 ጥሪ ያድርጉ
2. በዩናይትድ ኪንግደም (እንግሊዝ) ጥገኝነት ለመጠየቅ ከፈለጉ
የዩናይትድ ኪንግደም (እንግሊዝ) የጠረፍ ወኪል (መንግስታዊ ድርጅት)ን በስልክ ቁጥር 02081964524 ያግኙ
3. በዩናይትድ ኪንግደም (እንግሊዝ) ጠረፍ አልባን (ኖ ቦርደርስን) ለማግኘት ከፈለጉ
በስልክ ቁጥር 07902312730 ያግኙ (በፖለቲካ ንቁ ተሳታፊዎች እንጂ ጠበቆች አይደለንም)
ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (እንግሊዝ) ከደረሱና ጠረፍ አልባ አባሎችን (ኖ ቦርደርስን) እርስዎ ስላሉበት ሁኔታ ለማነጋገር ከፈለጉ፡
ይህንን ቁጥር መደወል ይችላሉ። ያስታውሱ እኛ በፖለቲካ ንቁ ተሳታፊዎች እንጂ ጠበቆች አይደለንም እንዲሁም ከመንግስት ጋር
ግንኙነት የለንም። አንዳንዶቻችን በደቡባዊ ለንደን ክራይዶን ከተማ እርስዎ ጥገኝነት ለመጠየቅ ከፈለጉ የሚሄዱበት አካባቢ
እንኖራለን። ስለ ጉዳይዎ ለመነጋገር ከፈለጉ እኛን ሊያገኙ ይችላሉ።
ጥገኝነት የሚጠይቁ ከሆነ እርስዎ ለምን በሃገርዎ ውስጥ ህይወትዎ አደጋ ላይ እንደወደቀ ብዙ አይነት ጥያቄዎችን ሊጠየቁ
ይችላሉ። ዝርዝር መረጃዎችዎ በሙሉ ትክክል መሆኑን ያረጋግጡ። ለምሳሌ : ቀኖች ፤ ስሞች እና አስፈላጊ ክስተቶችን ጨምሮ::
ስለዚህ በአጠቃላይ ምን አይነት መረጃ እንደሚሰጡ በጥንቃቄ ያስቡ።
ለበለጠ መረጃ ወደ ጠረፍ አልባ (ኖ ቦርደርስ) ጥሪ ለማድረግ በስልክ ቁጥር 07902312730 ይደውሉ::